ቤተማሪያም ግዛውም ከተመራቂ ተማሪዎች አንዱ ሲሆን አድማስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት አሰጣጥ  ጥራቱ ጥያቄ የለውም ይላል::በአካውንቲንግ ለሶስት ዓመታት ትምህርቱን ተከታትሎ በዚህ ዓመት ለመመረቅ የበቃው ተማሪ ቤተማሪያም ዩኒቨሬሲቲው ጥራትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው:: ከዚህ ጎን ለጎን ደረጃውን የጠበቃ ምዘና በመስጠት ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን አሰልጥኖ እያወጣ እንደሆነም ይመሰክራል