ትዕግስት ጸጋየ በበኩሏ ዩኒቨርሲቲው በልዩ ትኩረት ተማሪዎችን በመከታተልና ደረጃውን የጠበቀ ምዘና በማድረግ ሰልጥነው

የሚወጡ ተማሪዎች በሁሉም መልክ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ያደርጋል ትላለች፡፡ ቀደም ሲል ከሌላ ዩኒቨርሲቲ በሌላ ትምህርት የመጀመሪያ ዲግሪ እንዳላት የገለጸች ትዕግስት አድማስ ብቃት ያላቸውን መምህራን በመመደብ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ተማሪዎችን ለማብቃት የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውን ትናገራለች::

በማኔጅመንት የዲግሪ ተመራቂ የሆነችው ትዕግስት ኢሬና በበኩሏ አድማስን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ከሚለዩት መሰረታዊ ጉዳዮች አንዱ የመምህራን ብቃትና የምዘና አሰጣጥ ስርዓቱ ጠንካራ መሆኑ ነው ትላለች:: ትዕግስት አያይዛም በተለይ መምህራን ከተማሪዎቻቸው ጋር ያላቸው ቅርበት የጠበቀ በመሆኑ ከተማሪዎች የሚነሱ ችግሮችን በወቅቱ ለመፍታት ያስችላል ይህ ደግሞ  ለመማር ማስተናሩ መጠናከር የጎላ ድርሻ እንዳለው ትናገራለች::