አድማስ ኒቨርስቲ ከ1993 ዓ/ም አሰካሁን ድረስ ባለው ጊዜ ከ63 ሺህ በላይ ተማሪዎች በተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞች አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡ ባለፉት ሁለት አሰርት ዓመታት ባፈራው የሰው ኋይል እንደ አንድ የግል ተቋም የሚጠበቅበትን መወጣት ችሏል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ እስካሁን ድረስ አሰልጥኖ ያስመረቃቸው ዜጎች በአግሪቱ የኢኮኖሚ ግንባታ የበኩላቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

በአሁኑ ሰዓትም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እያሰለጠነ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው  ለትምህርት ጥራት በሰጠው ልዩ ትኩረት የውስጥ አደረጃጀቱን በማስተካከልና አሰራር በመዘርጋት ብቃት ያላቸው ዜጎችን ለማፍራት ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡

ባለፉት ተከታታይ ዓመታት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ባደረጋቸው ቀጣይነት ያላቸው ተግባራት ምክንያትም  በ2010 ዓ/ም የአዲስ አበባ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ቢሮ በከተማይቱ የሚገኙ የግል ኮሌጆችን በመከታተልና በመገምገም ደረጃ የማውጣት ስራን ያከናውናል፡፡ በተለይም የትምህረት ጥራት ያረጋግጣሉ ያላቸውን መስፈርቶችን በማውጣት  በከተማይቱ በሚገኙ 75 የግል የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ባካሄደው ዓመታዊ ግምገማ ስድስት ኮሌጆችን በከፍተኛ ደረጃ መርጧል፡፡

በአፈጻጸማቸውና ባላቸው የትምህርት አሰጣጥ ብቃት ከመረጣቸው ስድስት ኮሌጆች  መካከልም አምስቱ የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች ናቸው፡፡ ይህ የሚያስደንቅ ውጤት ነው፡፡ይህ ውጤት የተገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥራትን ለማረጋገጥ በሚያደርጋቸው ተከታታይ  ጥረቶች እንደሆነ እሙን ነው፡፡ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ በሰጠው ምስክርነት መሰረት የአድማስ ኮሌጆች ከሁሉም የግል ኮልጆች በተውጣጡ አመራሮች ተጎብኝተዋል፡፡ ይህ የዩኒቨርሲቲው የትምህርት አሰጣጥ ጥራት ደረጃ የሚሳይ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በዩኒቨርሲቲው ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነመበሩ ተማሪዎችስ ምን ይላሉ?

ተስፋዬ ታደሰ በአድማስ ዩኒቨርሲቲ ቢሸፍቱ ካምፓስ ላለፉት ሶስት ዓመታት በአካውንትንግ የድግሪ ፕሮግራም ትምህረርቱን ሲከታተል  ከቆየ በኋላ ሐምሌ 21 ቀን 2010 ዓ/ም በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የምረቃ ስነስርዓት ከተመረቁ 4 መቶ 90ተማሪዎች መካከል አንዱ ነው፡፡ ተስፋዬን ከሌሎች ለየት የሚያደርገው  በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቁ የዋንጫ ተመራቂ መሆኑ ነው፡፡ በዩኒቨርሲቲው የተመራቂ ተማሪዎች ፕሬዚደንት ሆኖም ሰርቷል፡፡

ተስፋዬ ስለ አድማስ ዩኒቨርሲቲ ሲናገር “አድማስን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ለየት የሚያደርጉት  ነገሮች  አሉት፡፡ ከእነዚህም መካከል በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው ለትምህርት ጥራት የሰጠው ትኩረት ነው፡፡“ ይላል፡፡

ለትምህርት ጥራት የሚያደርገው ጥረት የተለያዩ መገለጫዎች እንዳሉትም ተስፋዬ ይናገራል፡፡ “ዩኒቨሬሲቲው ብቃት ያላቸው መምህራንን በመመመደብ፣ ላይብራሪና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁሶችን በሟሟላት፣ የምዘና ስርዓቱን በማጠናከርና ተከታታይ ምዘና በመስጠት የትምህርት ጥራቱን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል::”

ተስፋዬ አያይዞም ዩኒቨርሲቲው ክትትልና ድጋፍን በማድረግ እንደዚሁም በተማሪዎች የሚነሱ ችግሮችን ባግባቡ በመረዳት በፍትነት በመፍታትና የተማሪዎች ለውጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ ያለውን ለውጥ በመከታተልና በመገምገም የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በማገዝ ረገድ የሚፈጽማቸው ተግባራት ዩኒቨርሲቲውን ተመራጭ ያደርገዋል ይላል::