ዳግም ከበደ

አዲስ አበባ (አዲስ ዘመን) – አድማስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ በሚገኙ ካምፓሶቹ በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ ትምህርት እና ስልጠና መርሃ ግብሮች 7ሺ 358 ተማሪዎችን ትናንት አስመርቋል።

ተማሪዎቹ በአካውንቲንግ፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በቢዝነስ ማኔጅመንት እና በሌሎች ትምህርቶች የተመረቁ ናቸው።

በኮኮብ አዳራሽ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ሞላ ፀጋይ የተማሪዎቹን መመረቅ አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት እንደተናገሩት፤ ዩኒቨርስቲው ላለፉት 19

ዓመታት በአገሪቷ የልማት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን የተማረ የሰው ሃይል በማሰልጠን ረገድ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።  ዘንድሮም ከ7 ሺ በላይ ተማሪዎች ከ1 ኛው ገጽ የዞረ ተመርቀዋል።

«ዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር ጥራቱን ከምንግዜውም በላይ ለመጨመር፤ በጥናት እና ምርምር ላይ አስተዋዕፆ ለማበርከት እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ያለውን ብርቱ እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላል» ያሉት ፕሬዚዳንቱ የዘንድሮው ተመራቂዎች፤ በተመረቁበት የሙያ ዘርፍ አገራቸውን በጥሩ ስነ ስነምግባር ማገልገል እንዲችሉ አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲው ባለፉት 19 ዓመታት በመደበኛ እና በርቀት ትምህርት፤ በዲግሪ፣ በዲፕሎማ በሰርተፍኬት ከ60 ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት በዲግሪ እና በቴክኒክ ሙያ በመደበኛውና በርቀት

ትምህርት በአገር ውስጥ እና በውጪ አገራት ( በሱማሌ ላንድ እና ፑንት ላንድ ) ከ30 ሺ በላይ ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል።