አድማስ ዩኒቨርስቲ በአዲስ አበባ በቢሸፍቱና በመቐለ በሚገኙ ካምፓሶቹ  ለ1 ሺሕ 1 መቶ 41  ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።    

የዩኒቨርስቲው የአስተዳደርና ፋይናንስ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን አማረ እንደገለጹት  ዩኒቨርስቲው ያለው የሰው ሃይል በየጊዜው ከፍና ዝቅ የሚል ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት  769 ቋሚና 372  የትርፍ ሰዓት መምህራን ዩኒቨርስቲው የፈጠረውን የስራ እድል ተጠቃሚ ሆነዋል።

አቶ ካሳሁን አያይዘውም አድማስ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎችና እርከኖች የተማረን የሰው ሃይል ከማፍራት ባኛገር ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር ረገድም ቀላል የማይባል ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡

ዩኒቨርስቲው ከተለያዩ ተቋማት ጋር የጠበቀ ግንኙነት በማድረግ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በቀላሉ የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ ይገኛል፡፡