የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ አንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ፡፡
- Posted by admin
- Posted in Admas News
በ2015 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ሐገሪቷ የምትፈልገውን ብቃት ያለው ምሩቅ ለማፍራት እንዲረዳ ታልሞ ረቂቅ የአፈፃፀም መመሪያ እንደተዘጋጀለት የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገለፁ፡፡
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከዩኒቨርሲቲዎች ፕረዚደንቶች ጋር በነበራቸው የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ረቂቅ ሰነድ ምክክር መድረክ ላይ ይህንን ማለታቸው ኢትዮጵያን ሞኒተር የበይነ-መረብ ጋዜጣ (https://ethiopianmonitor.com/…/ministry-to-introduce…/ የገለፀ ሲሆን ይህንኑ የምክክር መድረክ በሐገራችን በሚገኙ ሌሎች የሚድያ ተቋማት የዜና ሽፋን ሆኖ እንደነበርም ይታወሳል፡፡ በምክክር መድረኩ የትምህርት ሚኒስትሩ ሲገልፁም ሐገራችን የሚያስፈልጋት የተማረ የሰው ሐይል በእውቀት እና በሙያዊ ክህሎቱ የዳበረ ዜጋ መሆኑን ገልፀው ይህም በሁሉም የመንግስትና ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን እየተማሩ የሚገኙ ተመራቂ ተማሪዎች ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመውጫ ፈተናው ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ በየአመቱ ከ150 ሺህ በላይ ምሩቃን ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ሲሆን ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የመጀመርያ ዲግሪ ምሩቃን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተናውን መውሰድ ያለባቸው መሆኑና ይህም በሚኒስቴር መ/ቤቱ ካለው አጠቃላይ የለውጥ ሂደት አንድ አካል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በወቅቱም እንደ ኢቢሲ (EBC) ፣ ፋና ቴሌቪዥን እና ሌሎች በርካታ የመገናኛ ብዙኃን ይህንን ጉዳይ የዘገቡት ሲሆን በጥቂቱ የሚከተለውን መስፈንጠርያዎች በመንካት የዜናው ጥንቅሮች መመልከት ይችላሉ፡፡