የአድማሰ ዩኒቨርስቲ የቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጆች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2013 ዓ.ም ባደረገው የስታንዳርድ ኢንስፔክሸን 5ቱም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኮሌጆች ተሸላሚ ሆነዋል
- Posted by admin
- Posted in Admas News
የአድማሰ ዩኒቨርስቲ የቴክኒክ እና ሞያ ኮሌጆች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2013 ዓ.ም ባደረገው የስታንዳርድ ኢንስፔክሸን 5ቱም በአዲስ አበባ የሚገኙ ኮሌጆች ማለትም የመስቀል ካምፓስ (ቂርቆስ ክ/ከተማ) ÷ የመካኒሳ ካምፓስ (ን/ላ/ክ/ከተማ) ÷ የቃሊቲ ካምፓስ (አ/ቃ/ክ/ከተማ) ÷ የመገናኛ ካምፓስ (ቦሌ ክ/ከተማ) እና የምሰራቅ ካምፓስ ( የካ ክ/ከተማ) ደረጃ 3 ላይ የገቡ በመሆኑ የሰርትፍኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ በወድድሩ ደረጃ 3 ከገቡት 13 የግል ኮሌጆች ውስጥ የመስቀል እና መካኒሳ ካምፓስ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት የዋንጫ እና ሰርቲፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡ የአ/አ ከተማ አስተዳደር የትምህርት እና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን በ2013 ዓ.ም ባደረገው የዕውቅና ዕድሳት የተዘጋጀው ስታንዳርድ የአድማስ ዩኒቨርስቲ የመካኒሳ ካምፓስ የሶፍት-ስኪል ሥልጠና ከሚሰጡ የከተማው ኮሎጆች መካከል 1ኛ በመውጣቱ የዋንጫ እና ሰርቲፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል፡፡