አድማስ ዩኒቨርሲቲ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ ዎርክሾፕ እያካሄደ ይገኛል።

IMGL2713

አድማስ ዩኒቨርሲቲ በድህረ እና ቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች ላይ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ በዋሽንግተን ሆቴል ከትምህርት ሚኒስቴር፣ ከትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን፣ ቀጣሪ ድርጅቶች እና የዘርፉ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የ4 ድህረ-ምረቃ እና 9 የቅድመ-ምረቃ የትምህርት መስኮች እየገመገመ ይገኛል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ሞላ ፀጋይ (ፒኤችዲ) እና የዕለቱ የክብር እንግዳ ድንኳና ንጉሳ (ፒኤችዲ) ትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን (የቀድሞው ከከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ) የጥራት ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬከተር መርቀው የከፈቱ ሲሆን የክብር እንግዳው በመክፈቻ ንግግራቸውም }ዩኒቨርሲቲው የሚጠቀምበትን ስርዓተ-ትምህርት ከባለድርሻ አካላት ጋር ልማከርበት፣ ምን ይጨመርበት፣ ምን ክፍተት አለበት ብሎ ይህን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ በአግባቡ የተደራጀ የምክክር እና የስርዐተ-ት/ት ማፅደቅያ መድረክ ማዘጋጀቱ ለሌሎች የመንግስትም ሆነ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አርአያ የሚያደርገው ነው~ ሲሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል።በተያያዘም ይህ ባለድርሻ አካላትን ያካተተው የስርዓተ ትምህርት ግምገማና ማፅደቅያ መድረክ ውጤታማ ተማሪዎችን በማፍራት የቀጣሪ ድርጅቶችን ፍላጎት ማርካት እንዲሁም የስራ እድል ፈጣሪ የሆኑ ምሩቃንን ማፍራትን ያለመ ሲሆን ሎሎች ተጨማሪ ግብዓቶች እንደሚገኝበት ይታመናል፡፡

Leave us a Comment