አድማስ ዩኒቨርስቲ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስምሪት እና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጎበኘ።

==========================

ግንቦት 15 ቀን 2014 ዓ.ም፤ በኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ሥራ ስምሪት እና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በአድማስ ዩኒቨርስቲ በአካል በመገኘት የጉብኝት መርሃ-ግብር አካሂዷል።

በጉብኝቱ ለኮሚቴው ስለ መማር ማስተማር፣ ጥናትና ምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ የውስጥ የጥራት አጠባበቅ ስርዐት በተመለከተ በዩኒቨርስቲው ፕረዚዳንት፣ ም/ፕረዚዳንቶችና ሌሎች የስራ ሀላፊዎች ገለፃ ተደርጓል።

ከገለፃው በኋላ ኮሚቴው የግብአት ምልከታና የሰነዶች ምርመራ አካሂዷል።

በመጨረሻም ኮሚቴው የጉብኝቱን ውጤት ለተገኙት የማኔጅመንት አባላት በቃል ግብረ-መልስ ካቀረበ በኋላ በቀጣይ በፅሁፍ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

Blog Attachment

Leave us a Comment