አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክ እና ሙያ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

grad2014 banner

አዲስ አበባ፡ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አድማስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዲግሪ እና በቴክኒክ እና ሙያ ትምሕርት ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 4 ሺህ 551 ሰልጣኞች አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎች ውስጥ 68 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡

ዩኒቨርሲቲው፦ በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣ በሆቴል ማኔጅመንት፣ በኮምፒዩተር ሳይንስ እና በማርኬቲንግ ማኔጅመንት ነው ሰልጣኞችን ያስመረቀው።

የአድማስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሞላ ፀጋየ (ዶ.ር) እንዳሉት ዩኒቨርሲቲው በሶማሌ ላንድ እና ፑንትላንድ ተማሪዎቹን እያሰለጠነ ነው።

ዩኒቨርሲቲው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጥራት ዘርፍ ለ3 ጊዜ አሸናፊ መኾን መቻሉን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ከተማ በተደረገ የጥራት እና ይትምህርት ምዘና አድማስ ዩኒቨርሲቲ ሁለት ካምፓሶቹ የ2ኛ እና 3ኛ ደረጃን መያዛቸውን አስረድተዋል።

ዶክተር ሞላ ዩኒቨርሲቲው የኅብረተሰብ አገልግሎቱን ለማሳደግ እየሠራ ይገኛል ብለዋል። በቅርቡም በ3ኛ ዲግሪ ለማስተማር በፍቃድ ሂደት ላይ መኾኑን ተናግረዋል።

ምንጭ ፡ አማራሚዲያኮርፖሬሽን

Leave us a Comment