አድማስ ዩኒቨርሲቲ የቃሊቲ ካምፖስ 3ኛውን ዓመታዊ የጥናትና ምርምር ኮንፍረንስ አካሄደ።
- Posted by admin
- Posted in Admas News
ካምፓሱ ዛሬ ህዳር 17/2015 ዓ.ም “በቴክኖሎጂ የተደገፈ የስልጠና እና ትምህርት ጥራት” (Technology Supported Quality Education and Training) በሚል ርዕስ ዙርያ ነው።
በጥናትና ምርምር ኮንፍረንሱ የጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ዩኒቨርሲቲው ሰራተኞችና ተማሪዎች ተገኝቷል።
በጥናትና ምርምር ኮንፈረንሱ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በአድማስ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ተሳትፎ፣ የዩኒቨርሲቲ-ኢንዳስትሪ ትስስር ዳይሬክተር ተስፋዬ ሙህዬ (ዶ/ር) ሲሆኑ በንግግራቸውም አድማስ ዩኒቨርሲቲ በሚያደርጋቸው የጥናትና ምርምር ተግባራት፤ ግልፅ ዓላማ፣ ችግር ፈቺ እና በተጨባጭ ያሉትን ክፍተቶች የሚሞሉ መሆን ያለባቸው መሆኑን እና ለዚህም ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በመልዕክታቸው አክለውም አሁን በደረስንበት 21ኛው ክ/ዘመን፣ የትምህርት ጥራት ያለ ቴክኖሎጂ ድጋፍ ትርጉም እንደሌለውና ማሳካትም አዳጋች የሚያደርገው መሆኑን የተቃሱ ሲሆን ካምፓሱ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ ማዘጋጀቱ የሚያስመሰግነው ነው ሲሁ አክለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ ሶስት ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የመዝጊያ ንግግርና ለመድረኩ ስኬት አስተዋፅኦ ለነበራቸው አካላትም በአድማስ ዩኒቨርሲቲ የቃሊቲ ካምፓስ አቶ ናትናኤል ስዩም የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።