አድማስ ዩኒቨርሲቲ ቢሾፍቱ ካምፓስ ላለፉት ተከታታይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን 4 መቶ 90 ተማዎችን በዲግሪና በቴክኒክና ሙያ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በዛሬው ዕለት በደማቅ ሥነሥርዓት አስመረቀ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ማዕከላዊ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ዳይሬክተር አቶ ተፈሪ ክብረት ለፍኖተ አድማስ እንደገለጹት ከተመራቂዎቹ መካከል 2 መቶ 45 ፣ በዲግሪ፣ 2 መቶ 45 ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት መርኃ-ግብሮች የሰለጠኑ ናቸው፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም የቢሾፍቱ ካምፓስ እስከ አሁን ድረስ 1 ሺህ 2 መቶ 42 በዲግሪ መርኃ-ግብር በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ፣   በቢዝነስ ማኔጅመንት፣ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ኮሚኒኪሽን ቴክኖሎጂ እና  በኮምፒዩተር ሳይንስ 3 ሺህ 7 መቶ 95 ደግሞ በቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና በተለያዩ የሥልጠና ዘርፎች ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ 5 ሺህ 37 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡